እንዴት ነው


አቶ ጆይ ሚዲያ ዌብሳይት አናጺው እንዴት ነው ሳይት የሚያንጸው?

ሀ. ዘና ብሎ »

ለ. ተባብሮ » 

ሐ. ተመካክሮ »

መ ወጥኖ »

 

ሀ. ዘና ብሎ


የዌብሳይታችን ሳሎን ጓዳ ዘወርወር ብለው  እንዳዩት የቢዝነስ አማርኛ ብዙ የለንም።የቤተሰብ ፣የቤተዘመድ አማርኛ ነው ያለን።

ምን ለማለት ነው ?

በምንሰራው ስራ ተደስተናል ለማለት ነው።ገና ስራዉን ሳንሰራ ተደስተናል ለማለት ነው።እርስዎንም ስናናግር ረጋ ብለን ነው

እርስዎም እኛን ሲያናግሩን ዘና ብለው ረጋ ብለው ነው።

ተደስተዋል ማለት ነው።

በምንሰራው ስራ ደግሞ ስለምናምንበት ደስ የሚል ነገር አለው  -የቸርች ወይም የአማኝ አገልግሎት መስጠት አንዳች ደስታ የለውም ይላሉ  ወይ?

አቶ ጆይ ሚዲያ ደግሞ ስነጽሁፍ አርት ኪነ-ስነ ጥበብ ስለሚወድ እንደየአገባቡ ለስላሳ አካሄድ(ሜትድ ወይም ሜቶድ ወይም ሜቶዶሎጂይ) ይጠቀማል።

ክርር ባለ የቢዝነስ እንግሊዝ-አማርኛ ያናግሩኝ ካሉም እ... እንደሱም ይቻል ይሆን ይሆናል።

.ተባብሮ


እያንዳንዱ ሰው የራሱ ችሎታ አለው።

አንዳንዱ ጎበዝ አናፂ ነው ።ሌላው ሁነኛ ገንቢ ነው ሌላው ደግሞ  ጎበዝ ቀለም ቀቢ ነው ።ደሞ አለ ሌላ ግሩም መሰረት መስራች ።ይመጣል ደግሞ ሌላው  መልካም የሆነ የኮርኒስ እና የጣሪያ ስራ የሚችልበት ።የቧንቧ ሰራተኛ አለ ፣አጥር የሚያጥር አለ።

ደግሞ ሌላው ይመጣል ደስ የሚያሰኝ ሰዎችን የመንከባከብ ችሎታ ያለው።

እነዚህን ሁሉ የሚያስተባበር ደግሞ አለ።

ፕሮግራመሮች አሉ ፣ግራፊክስ ዲዛይነሮች አሉ፣ዳታቤዝ የሚያዋቅሩ አሉ ፣የኔትወርክ መስመር የሚዘረጉ አሉ ፡ዶሜይን እና ሆስቲንግ ሰርቪስ የሚያመቻቹ አሉ።

ሥራውን በባለቤትነት እና በኃላፊነት የሚሰሩ አሉ።

እንዚህን ሁሉ ቴክ ኖ ሎ ጂ ካል ቴክኒክ እና ታክቲክ በመጠቀም አንድ ሰው ሊሰራቸው ይችላል።

ሁሉም እንደ አገባቡና እንደ ሁናቴው ነው።

በተለያየ  የዓለም ክፍል ከሚገኙ የስራ ወዳጆቻችን ጋር ተባብረን ነው የምንሰራው ለማለት ነው::


ሐ. ተመካክሮ


የዌብ ሳይት ግንባታ ስራ አንዱ ባህሪው - ያቀራርባል። ታዲያ መቀራረብ ጥሩ ነገር አይደለም እንዴ ? ሳናስበው ጥሩ የስራ ወይም የአገልግሎት ጓደኛሞች  ልንሆን እኮ ነው።

ልምድ እንደሚነግረን - አንዴ ስራው ከተጀመረ -ሥራው ካለቀ በኋላም-  የዛሬ ወርም በመንፈቅም በዓመቱም የሚጨመር የሚቀነስ የሚታደስ  ነገር ስላለው በጥሩ የስራ ግንኙነት አብረን እንዘልቃለን ማለት ነው።

እርስዎ የሚያመጡት ሃሳብ እና የሚያቀርቡት ኢንፎርሜሽን ነው ስራውን ወደፊት የሚያራምደው።

አቶ ጆይ ዌብ ሚዲያ ስራውን የሚሰራው ከእርስዎ ጋር መክሮ ተማክሮ ነው።

አንዴ ስራው ከተጀመረ ብዙ ኢሜይል ሊልክልዎት ይችላል - “እባክዎ ፎቶ ይላኩ” ፣ “እባክዎ ሎጎ አሜይል ያድርጉ”፣ “የድርጅትዎ ዓለም አቀፉ አድራሻ ምን እንዲሆን ይወዳሉ- ደብልዩ ደብልዩ ዶት እኮ …  ዶት ኮም ይሁንልኝ ያሉትን ሰምቻለሁ ፣ይሁንልኝ ካሉም ይሆናል ዳሩ ግን ዶት ኮም እኮ ለኮሜርስ ወይ ለንግድ ነው ዶት ኦርግ ወይም ዶት ኔት ቢሆን አይሻልዎትም ወይ?” እያለ ይጠይቅዎታል… ያማክርዎታል።

መ. ወጥኖ »


ምንድነው የሚወጥነው ?

አቶ ጆይ ሚዲያ ፕሮግራመር ባይሆንም ወሳኝ ፕሮግራመር ባልንጀሮች አሉት።

ይህ ብቻ አይደለም አቶ ጆይ ሚዲያ  ለሕንጻ ግንባታ የሚያስፈልጉ ያናጺ ዕቃዎችን ያውቃል።

ይመስገን በዚህ ዘመን ቤት መቀለስ ቀሏል - ወይስ አልቀለለም?

እርስዎ እራስዎ ቤትዎን ሊቀለብሱ ይችላሉ።

እንግዲህ የአቶ ጆይ ሚዲያ አፕሮች ሁማኒስቲክ ኣፕሮች ይሰኛል ።

እንደምን ያለ ነገር ነው ይህ  ሁማኒስቲክ ኣፕሮች ?

በታክቲክ እና በቴክኒክ በቀለም እና በድምቀት አሸብርቆ ከሚታይ ቤተ-ገጽ(ሆምፔጅ ለማለት ነው) ይልቅ ቀለል ብሎ ለሰዎች ጠቀሜታው የጎላ ሕንጻ ማቅረብን ያመለክታል።

ይህ ብቻ አይደለም አቶ ጆይ ዌብ ሚዲያ አብያተ ክርስቲያናት የኢንተርኔትን ዓለም ሰርከም_ናቪጌት* እያደርጉት ነው ወይብሎ ይጠይቃል።

(ሰርከም_ናቪጌት* ሲል እያሰሱት (እየጎበኙት) ነው ወይ?  ለማለት ሳይሆን እየበዘበዙት ነው ወይ? ኮሎናይዝ እያደረጉት ነው ወይ ? ባንዲራቸውን እያውለበለቡበት ነው ወይ?ለማለት ነው)

እንግዲህ ቤት ሲቀለበስ accessibility, usability, functionality …ወዘተ ተሰኙ ነገሮች አሉ ። እነዚህን ከግንዛቤ ማስገባት ሊጠቅም ይችላል።

ኢንቴሌክቿል ፕሮፐርቲይ ስለሚሉትስ ነገርስ አልሰሙም እንዴ?

መቸም እኛ ማህበረሰባችን ማህበረሰባዊ ስለሆነ -ይመስገን- ያለውን በነጻነት ከፍሎ ተካፍሎ አካፍሎ ነው የሚኖረው

ታዲይ ይህ ኢንተርኔት ላይ የወጡ ፎቶዎችን እና ሌሎችንም ሀብቶች (ሪሶርሶች ለማለት ነው) ያካትታል ።

ታዲያ እዚህ ጋር ነው አቶ ጆይ ሚዲያ የሚያግዞት። አስቀድሞ ግን አንድ የተከሰት ክስተት ይነግርዎታል።

አንድ ቤተክርስቲያን በሀገረ እንግሊዝ ዌብሳይት ሲያሰሩ ከኢንተርኔት ላይ ደስ የተሰኙበትን ፎት አገኙና ይህ ፎቶማ ለሳይታችን ሁነኛ ነው ብለው ተጠቀሙት።

ደግ ኣደረጉ ወይ?

ከለታት አንድ ቀን የፎቶው ባለቤት ባጋጣሚ ይሁን ሰው ነግሮት አይታወቅም የቸርቹን ዌብሳይት ሲጎበኝ እርሱ ያነሳው ፎቶ ከቸርቹ ዌብሳይት ጋር ተጣጥሞ ያገኘዋ

ከሰሳቸው በእንግሊዝ ፍርድቤትም አስቀጣቸው።

እባክዎ ይህን አርቲክል ያንብቡ::

አቶ ጆይ ሚዲይ እንዲህ እና ሌሎችም ተመሳሳይ ነገሮች እንዳይከሰቱ ያማክርዎታል።

እንነጋገር ካሉም እንነጋገር።